Skip to main content

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች መልካም ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት መድረክ ተካሄደ፡፡

image news

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች መልካም ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበትና በቀጣይ የሚደረግላቸውን ድጋፍ በተመለከተ ከመንግስት ጋር የሚመካከሩበትን መድረክ ማካሄድ መጀመሩ ተገለፀ ።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማን ጨምረው በሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ላይ ስራ የተፈጠረላቸው ወጣቶች የልምድ ልውውጥና ቀጣይ የሚደረገው ድጋፍ ዙርያ የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል ።

በመድረኩ መንግስት በግብርና ዘርፍ ፤ በኢንዱስትሪ ዘርፍና በአገልግሎት ዘርፎች ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የሚገልፅ ሪፖርት በየደረጃው እየቀረበ ይገኛል ።

በመቀጠልም ወጣቶች በልምድ ልውውጥ ያገኙትን ተሞክሮና ለቀጣይ መንግስት እንዲያደርግላቸው የሚፈልጉትን ድጋፍ በተመለከተ በመመካከር የጋራ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል ።