"በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ!" በሚል መሪ ሀሳብ የሥራና ክህሎት ቢሮ ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ስሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
ለሲዳማ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት ለብልፅግና ፓርቲ አባላት "በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ!" በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል ።
በማጠቃለያው ላይ በሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ስልጠናው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከመፍጠር በተጨማሪም የመፈጸምና የማስፈፀም አቅማን ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም አንስተው የሰለጠኑና የበቁ ወጣቶችን የስራ ዕድል በመፍጠር ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልገናል ብለዋል።
ሃላፊዋ አክለውም ዛሬ ከስልጠና ያገኛችሁትን እውቀት ተግባራዊ በማድረግና ጥራት ያለዉ ዘላቂና ቋሚ የስራ ዕድል በመፍጠር የወጣቶችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተግተን መስራት ያስፈልገናል ካሉ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫን ጠቁመው የስራ መመሪያ ከሰጡት በኋላ መድረኩ ተጠናቋል ።